Fana: At a Speed of Life!

ኮሮና ቫይረስን መከላከል ላይ የሚስተዋለው መዘናጋት በፍጥነት ሊታረም ይገባል-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በህብረተሰቡ ዘንድ ኮሮና ቫይረስን መከላከል ላይ የሚታየው መዘናጋት በፍጥነት ሊታረም እንደሚገባ  የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አሳሰቡ፡፡

በክልሉ ባለፉት ጊዜያት የኮቪድ-19 መከላከል ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና እና ምስጋና የተሰጠበት መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅም የመከላከያ ሰራዊት ለሀገሩ ሲባል ግንባሩን ለጥይት እንደሚሰጥ የጤና ባለሙያዎችም ለሌላዉ ዜጋ ሲባል ቤተሰቦቻቸውን ትተው ህይወታቸውን እስከመስጠት ድረስ መስራታቸውን አቶ ደስታ አንስተዋል፡፡

ባለሙያዎቹ በዚህ ደረጃ እየለፉ ቢሆንም  ህብረተሰቡ ግን  የእነሱን ልፋት መና የሚያስቀርና ለሀገር አደጋ በሚያጋልጥ መልኩ የኮሮና መዘናጋት በሁሉም ቦታ እየታየ ነው ብለዋል።

ስለሆነም እንደ አዲስ እየተስፋፋ የመጣውን  የኮሮና ሻይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ከመዘናጋት በመውጣት መረባረብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው÷ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሳይስተጓጎል ኮቪድን በመከላከል ረገድ አመርቂ  ስራ መከናወኑን አውስተዋል፡፡

በዚህም በባለሙያዎችና ሌሎች አካላት በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ወረርሽኙ  አስከፊ አደጋ እንዳያስከትል ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

አሁን የሚስተዋለው መዘናጋት ያስቀረነውን አደጋ እንዳይቀለብስ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡

በዛሬው እውቅና አሰጣጥ  መርሃ ግብር ላይ  በክልሉ ኮሮናን ለመከላከል ርብርብ ላደረጉ የህክምና ባለሙያዎችና  አጋር አካላት ተመስግነዋል፡፡

ቅናው የሰርተፊኬትና የዋንጫ ሽልማት ሲሆን÷ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለግለሰቦችና ለተቋማት አበርክተዋል።

በክልሉ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 173 የሚሆኑ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ 8 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

 

በጌታቸዉ ሙለታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.