Fana: At a Speed of Life!

ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ በገላን እና ሆለታ ከተሞች እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሸባሪው ሸኔን የሚቃወም ሰልፍ በገላን እና ሆለታ ከተሞች እየተካሄደ ነው።
የገላን እና ሆለታ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ሀገሪቱን ለማፍረስ የፈጠሩትን ጥምረት አውግዘዋል።
ሰልፈኞቹ ሸኔ የኦሮሞን ስም ሽፋን በማድረግ ከህወሓት ጋር መሰለፉ አዲስ ባይሆንም የሀገር ጠላት መሆኑን በተጨባጭ ያረጋገጠበትን ተግባር ነው የፈፀመው ብለዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ እና የሀገር ጠላት ነው፣ ሸኔ የወያኔ ተላላኪ እና ከሀዲ ነው የሚሉ መፈክሮችን በመያዝ ድርጊታቸውን አውግዘዋል፡፡
የሆለታ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ ፀሀይ ዘለቀ፥ የሆለታ ህዝብ የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር ከመቼውም በላይ ቁርጠኛ ናቸው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.