Fana: At a Speed of Life!

በኬንያ ሲሳተፍ የነበረው የአትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ በነበረው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲሳተፍ የነበረው የአትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

በ12 ሜዳልያዎች 4ኛ ደረጃ ከዓለም በመያዝ ያጠናቀቀው ልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ የተመራ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለቡድኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡

የኮሚቴው አባላት እንዲሁም የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰለች መልካሙ በማህበሩ ስም ለልኡኩ ጉንጉን አበባ ማበርከታቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወይዘሮ አበባ ቡድኑ ባስመዘገበው ውጤት መኩራታቸውን ገልፀው÷ ‘‘እንኳን ደስ አላችሁ ፤ እንኳን በድል ተመለሳችሁ’’ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.