Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የመከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ተመላሽ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ለህልውና ዘመቻ የሃገር ጥሪን በመቀበል መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ተመላሽ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሽኝት ተደረገ፡፡
 
በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሃመድ ቡህ÷ከአባቶቻችን የተረከብናት ሃገር በህወሓት ሽብርተኛ ቡድን እንድትፈርስ ፈጽሞ አንፈቅድም ብለዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑን አደብ ለማስገዛትና ሃገርን ለትውልድ ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስተላለፍ ዳግም ለሃገራዊ ግዳጅ በመዝመታችሁ አስተዳደሩ ታላቅ አክብሮት አለው፤ በታሪክም ሲታወስ ይኖራል ነው ያሉት፡፡
 
የአስተዳደሩ ፍትህ ጸጥታና ህግ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ ጣሀ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ከውስጥ እና ከውጭ የተደቀናበትን ጠላትና ችግር አሸንፋ እንድትወጣ ልጆቿ ድሬደዋን ጨምሮ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል የህልውና ዘመቻውን መቀላቀላቸውን አንስተዋል፡፡
 
ተመላሽ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ግንባር በማቅናት በድል የሃገራችሁን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ እንደምታደርጉ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
 
በሽኝት መርሃ ግብሩ የአስተዳደሩ ከንቲባ ለተመላሽ የሰራዊት አባላት የሃገርን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ማስረከባቸውን ከድሬዳዋ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.