Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ ቴሌኮም የደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን በደቡብ ክልል ሰባት ዞኖች ለሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የሪጅኑ ኃላፊ አቶ ሹሜ አብሽሮ ተቋሙ በማህበረስብ አገልግሎት በርካታ ተግባራትን እንያከናወነ መሆኑን ገልፀው ÷ የዛሬው የድጋፍ መረሃ ግብር የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በተሰማሩበት የትህምርት መስክ ጠንክረው ሊማሩ እንደሚገባ ያመላከቱት ሃላፊው ተመሳሳይ ተግባራት በቀጣይም እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ መርክኔ ማለዳ ኢትዮ ቴሌኮም በሁለንተናዊ ማህበራዊ ዘርፍ ከዚህ ቀደም በርካታ ተግባራትን የሠራ መሆኑን አስታውሰው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ ድጋፉ በክልሉ ዳውሮ ፣ደቡብ ኦሞ ፣ኮንሶ ፣ጎፋ ፣ ሀዲያ እና ጉራጌ ዞኖች መደረጉ ተገልጿል፡፡

በማህሌት ኡኩሞ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.