የአየር ንብረት ለውጥ አደጋን ለመቀነስ የድንጋይ ከሰል ፕሮጀክቶችን ድጋፍ አቆማለሁ – ቻይና
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ቻይና በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የድንጋይ ከሰል ፕሮጀክቶች የምታደርገዉን የገንዘብ ድጋፍ ልታቆም መሆኗን አስታውቃለች፡፡
ቻይና ኢንዶኖዠያ እና ባንግላዲሽን ጨምሮ በሌሎች ታዳጊ ሀገራት የሚገኙ የድንጋይ ከሰል ፕሮጀክቶችን በገንዘብ ስትደግፍ መቆየቷን የቻይናዉ ፕሬዚዳንት ዥ ዢፒንግ ተናግረዋል፡፡
የቻይና መንግስት በካርቦን ልቀት ዙሪያ የተደረሰዉን የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት እንደምታከብር ፕሬዚዳንት ዥ ገልጸዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ እያጋጠመ ያለዉን የአየር ንብረት ለዉጥ ከግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ነው ቻይና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን ልታቆም መሆኗን ፕሬዚዳንቱ ያስታወቁት፡፡
ይህ ዉሳኔም ታዳጊ ሃገራት የሚያደርጉትን የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት እንደሚያግዝም ነው የተገለፀው፡፡
ከዚህ በፊት ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን በካርቦን ልቀት ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም ማሳየታቸዉ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡- አልጄዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!