በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ የተከለከለ ነው- ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በመስቀል በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በበዓላት ወቅት የሚተኮሱ ርችቶችን ሽፋን በማድረግ ሰላምን የማደፍረስ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች በህገ-ወጥ መንገድ የገዙትን የጦር መሣሪያ እንደሚፈትሹና የተለያዩ የፀጥታ ስጋቶችን እንደሚፈጥሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የህገ-ወጦቹን ድርጊት ለመከላከል እንዲቻልም መስከረም 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓልም ሆነ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳያገኝ ርችቶችን መተኮስ እንደማይችል ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ከዚህ ቀደም ፖሊስ ያስተላለፈውን መልዕክት በመተላለፍ ርችት የተኮሱ ግለሰቦች ተይዘው በፍርድ ቤት በዋስ መለቀቃቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!