Fana: At a Speed of Life!

በዴዴሳ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡኖ በደሌ ዞን ዴዴሳ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው የደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-80032-ኢት የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ በመገልበጡ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ዲቪዥን አስተባባሪ ኢንስፔክተር በኃይሉ ገዛኸኝ ገልጸዋል።

ተሽከርካሪው ሰዎችና እህል ጭኖ ከበደሌ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንዳለ በወረዳው መዲና ደምቢ ሲደርስ መገልበጡንም ተናግረዋል።

በአደጋው ሾፌሩን ጨምሮ ተሳፍረው የነበሩ አራት ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ የሟቾችንም አስከሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በወቅቱ በመንገድ ላይ የነበረና በተሽከርካሪው ተገጭቶ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት አንድ ታዳጊ ወጣት በወረዳው ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.