Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1ሺህ 496ኛው መውሊድ በዓል አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፏል።
የዘንድሮ መውሊድ በዓል አገራችን ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የገጠሙንን ፈተናዎችን በህዝቦቿ ጠንካራ አንድነትና ትብብር እየተመከተ ባለበት ወቅት መሆኑ እንዲሁም አገራዊና ክልላዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ በጀመርንበት ወቅቱን ልዩ ያረገዋል።
ስለሆነም በዓሉን ስናከብርም አገራዊ አንድነት ሊያጠናክሩና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የተጀመሩ ሁሉ አቀፍ ድጋፎችና ትብብሮችን ማጠናከር በሚችሉ መልኩ ሊሆን ይገባል።
ህዝበ ሙስሊሙ 1496ኛው መውሊድ በዓል በኃይማኖቱ አስተምህሮት መሠረት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በማገዝ እና የተለመደው ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን በሚያጠናክር መልኩ ሊያከብር ይገባል ነው ያለው።
ከዚህ በተጨማሪም ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ የሚገኘውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከልና የጥንቃቄ መመሪያዎች በመተግበር ሊሆን ይገባል ብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.