Fana: At a Speed of Life!

119 ኪሎ ግራም አደንዛዥ እጽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጉጂ ዞን የአዶላ ሬዴ ወረዳ በሞተር ብስክሌት ሲጓጓዝ የነበረ 119 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዱልከሪም ሁሴን እንደገለጹት፤ አደንዛዥ እጹ የተያዘው ምሽት ላይ ወደ ነገሌ ከተማ ሲጓጓዝ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ነው፡፡

የሞተር ብስክሌቱ አሽከርካሪ ለጊዜው ሞተሩንና አደንዛዥ እጹን ጥሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ለመያዝ ክትትል እየተደረገበት መሆኑም ተገልጿል።

የወረዳው ህዝብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረቡት ኢንስፔክተር አብዱልከሪም፤ ህገ ወጦችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ትብብር እንዲቀጥልም አስታዉሰዋል።

የወረዳው ፖሊስ ሀሰተኛ የብር ኖት፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያ እና አደንዛዥ እጽ ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ላይ እንደሚገኝም መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.