Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሞ ወጣቶች እና ህዝቡ ጁንታውን ለመቅበር የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የኦሮሞ ወጣቶች እና ህዝቡ ጁንታውን ለመቅበር የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ።
የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሃላፊ፣ አቶ ፈቃዱ ተሰማ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኦሮሞ ወጣቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በከፈሉት ውድ መስዋእትነት የመጣውን ለውጥ ለማጨለም ተላላኪዎቹን ጭምር በመጠቀም ጁንታው እየሰራ ነው ብለዋል አቶ ፈቃዱ።
በመሆኑም ጣረሞት ላይ የሚገኘውን ጁንታ ለመቅበር የኦሮሞ ወጣቶች ከሌሎች የክልሉ ህዝቦች ጋር በመሆን አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ተላልፏል።
በተጨማሪም የውስጥ ባንዳን በማፅዳት የፀጥታ ሀይሉን በመረጃ በመደገፍ በቂ እገዛ በማድረግ ለውጡን ካመጡትና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ ከቆሙ ወገኖች ሁሉ ይጠበቃል ነው ያሉት።
የኦሮሞ ወጣቶችና መላው የኦሮሞ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር ወጣቶች ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉም ጥሪ ቀርቧል።
ቡድኑ የመላ ኢትዮጵያውያን ጠላት መሆኑን ስላረጋገጠ አምርሮ መታገል ይጠይቃል ያሉት አቶ ፍቃዱ በዚህ ሂደት የኦሮሞ ህዝብ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people standing and people sitting
0
People reached
1,179
Engagements
Distribution Score
Boost Post
906
219 Comments
54 Shares
Like

 

Comment
Share
May be an image of 1 person, standing and text that says 'etv'
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.