ህወሓትን ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የደባርቅ ነዋሪዎች ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪውንና ወራሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
በደባርቅ ከተማ አሸባሪውን እና ወራሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ከአማራ ክልል መንግስት የቀረበውን ጥሪ አስመልክቶ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በዚህም የከተማዋ ነዋሪዎች የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለመደምሰስ ወደ ግንባር ለመዝመት የቀረበላቸውን ጥሪ መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡
የደባርቅ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ÷ ወራሪው ህወሓት ባሳለፍነው ነሀሴ ወር መጨረሻ ደባርቅ አካባቢ መጥቶ በጸጥታ ኃይሉ እና በወጣቱ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ የተረፈው እግሬ አውጭኝ ብሎ መፈርጠጡን አስታውሰዋል፡፡
“ዛሬም እንደ ትናንቱ ካለበት አቅራቢያ የወረዳችን ህዝብ አነቃንቀን ድል እናደርገዋለን” ነው ያሉት፡፡
የደባርቅ ከተማ ብልፅግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መብራቱ ሙሉጌታ በበኩላቸው÷ የህልውና ዘመቻውን ጥሪ ለተቀበሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
“አደረጃጀታችን አጠናክረን የተቃጣብንን የህልውና ዘመቻ እንመክታለን” ሲሉ መናገራቸውንም ከደባርቅ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!