Fana: At a Speed of Life!

አገርን ለማፍረስ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የሚሰሩ አካላት እጃቸውን እንዲሰበስቡ መንግስት አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገርን አንድነት ለመሸርሸር ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የሚሰሩ አካላት እጃቸውን እንዲሰበስቡ መንግስት ማሳሰቢያ ሰጠ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ የአሸባሪው ህወሓት ኃይል ኮምቦልቻ ከተማ ሰርጎ በመግባት ዛሬ ሌሊት ከ100 በላይ የከተማዋን ወጣቶች አሰልፎ መጨፍጨፉን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ፥ በማኅበራዊ ሚዲያ ሕዝብ እና መንግሥትን ለመከፋፈልና የአገሪቷን አንድነት ለመሸርሸር ከአሸባሪው ጋር የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
መንግስት በአገር አንድነትና ህልውና ላይ የመጡ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህም ቀጣይነት የሚኖረው ተግባር መሆኑን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
መንግስት እንደተዳከመ አድርገው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ትክክል አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ፥ መንግስት አሸባሪውን የህወሓት ቡድን መመከት የሚያስችለው ሙሉ ቁመና እንዳለው ነው የገለጹት።
አሸባሪው ህወሓት በያዛቸው አካባቢዎች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ደጀን የሆነው ሕዝብ እስከሚደርስላቸው ድረስ ተጋድሏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and text that says '.ዴሪ RE G መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግ ernment nication Servi FANA etv'
0
People reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.