Fana: At a Speed of Life!

የህልውና ዘመቻውን ከተቀላቀሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አንደበት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ረዳት ፕሮፌሰርነቱን ለማጸደቅ ቀናት ሲጠባበቅ የነበረው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ መምህሩ ሲሳይ እባብየና በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ኢንጂነሪንግ መምህር ኢንጂነር መንግሥት ካሳው የህልውና ዘመቻውን ተቀላቅለው ግንባር ነው ያሉት።
ሁለቱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ሥራና ቤተሰባቸውን ትተው ለአንድ ዓላማ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ተሰልፈው በግንባር ጠላትን እየተፋለሙ ነው።
ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት ላይ የተሰጠውን ግዳጅ ፈጽሞ ጁንታው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረሱ ከክፍለ ጦሩ አመራሮች የሻምበልነት ማዕረግ የተሸለመው መምህር ሲሳይ፤ እኔም ከጀግና ጋር ውዬ ጀግና ተብያለሁ ይላል።
ከማዕረጌ ጋር የተሸለምኳትን ታጣፊ ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዤ ከሎጂስቲክስ እስከ ግንባር የደረሱ ግዳጆችን እየተወጣሁ እገኛለሁ ሲል ተናግሯል።
የዩኒቨርሲቲ መምህርነት ሥራም ሆነ የተመቻቸ ኑሮ ማግኘት የሚቻለው አገር ስትኖር ነው የሚለው መምህር ሲሳይ፥ አገርን ለማፍረስ ህዝብን ለመጉዳት ሊወረን የመጣውን ጠላት ለመፋለም ብዕሩንም ጠመንጃውንም ይዞ መነሳቱን ይናገራል።
ጁንታው የሚፈጽመውን በደል በመቃወም በግንባር መሰለፍ የሚጠይቀው ሰው መሆን ብቻ ነው።
ለዚህም ቁርጠኛ ሆነን ግዳጅ እየፈጸምን ነው፤ ሠራዊቱም ቦታ በመምራት፣ በመዋጋትና በሙያው ጭምር በማገዝ አገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጾልናል።
ለጊዜው የዩኒቨርሲቲ መምህርነቴን ትቼ ለሀገሬ ግንባር ድረስ ሄጀ መታገል እፈልጋለሁ ሲል በርካቶች አፊዘውብኝ ነበር፤ ቤተሰቤም እውነት አልመሰላቸውም የሚለው መምህር ሲሳይ፥ ለአገሩ ሲል አፈር ለብሶ፣ ብርድና ቁር ከማይበግረው መከላከያ ሠራዊት ጋር አብሬ መታገል በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ብሏል።
ከዚህ በኋላ የጄነራልነት ማዕረግ እስከማገኝና የጁንታው ቡድን እስከሚወገድ ድረስ ትግሌን አላቋርጥም ማለቱን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.