Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተላለፉ ዋና ዋና መመሪያዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የተለያዩ መመሪያዎችን አስተላልፏል፡፡

ከዋና ዋና መመሪያዎች መካከልም፡-

1. አዲስአበባ ዉስጥ የሚኖር ማንኛውም ነዋሪ በእጁ የሚገኙ መሳሪያዎችን “ከዚህ ቀደም ያስመዘገበም ሆነ ያላስመዘገበ ” ዛሬን ጨምሮ በሁለት ቀን ዉስጥ በአቅራቢያው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲያስመዘግብ ፤

2. መላው ነዋሪ በብሎክና በመንደር ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መጠበቅ፣ መቆጣጠር አለበት።

3. የፀጥታ ሀይሎች ፤ የህብረተሰብ ፖሊስና የደንብ ማስከበር አደረጃጀቶች ከመደበኛው የፀጥታ ሀይል ጋር ተቀናጅተው ይሰራሉ።

4. የተለያዩ ድንገተኛ ፍተሻዎች ይካሄዳሉ፡- በመኖሪያ ቤት ፤ በኬላ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች ዉስጥ ድንገተኛ ፍተሻ ይካሄዳል ፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቀናነት ለዚህ ተባባሪ መሆን አለበት ፤ የመኖሪያ ቤት ፣ የሆቴል ፣ የማረፊያ አገልግሎት ሰጪ አከራዮች የሚያከራዩትን ግለ ሰብ ህጋዊ መታወቂያ መጠየቅ ፤ ኮፒዉን በአግባቡ ማስቀመጥ ይገባል።

5. በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ፤

6. የግልና የመንግስት የጥበቃ ኤጀንሲዎች ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ፤

7. ሰላማችንን ከማረጋገጥ አንፃር እስከአሁን የአዲስአበባ ወጣቶች በሰራዊቱ ዉስጥ ተቀላቅለው አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነዉ፤ አሁንም የከተማው ወጣቶችን በመመልመል የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ ተደራጅተው ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት እንዲጠብቁ ይደረጋል።

8. በመንግሥት እና በህዝብ መካከል ክፍተትና መጠራጠር እንዲፈጠር በሚሰሩ አካላት ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፤ በመሆኑም በዚህ ተግባር ዉስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ማንኛውም አካል ከወዲሁ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ፤

9. የአዲስአበባ የፀጥታ ተቋማት ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት ተናበው እየሰሩ መሆኑ ፤

10. ህዝቡ እያደረገ ያለዉ ድጋፍ የሚደነቅ ነዉ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.