Fana: At a Speed of Life!

በኮሪያው የግብርና ማሽነሪ ኩባንያ የተዘጋጀው አውደ ርዕይ በዱከም ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሪያው ኢኮስ ስቲል ሚል አስተባባሪነት የተዘጋጀው የኮሪያ የግብርና ማሽነሪ አውደ ርዕይ በዱከም ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡

አውደ ርዕዩ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ነው የተከፈተው ፡፡

አውደ ርዕዩ የኮሪያን የግብርና ቴክኖሎጂ በዘርፉ ለተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ተበሏል፡፡

በመክፈቻ ስነ ስዓቱ ላይ የግብርና ማሽነሪዎችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ዕቅድ ተይዞ እንደሚሰራ መገለጹን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.