Fana: At a Speed of Life!

የአባቶቻችን የድል አድራጊነት ታሪክ በእኔና በእናንተ ይደገማል እንጂ አይበላሽም-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከሃዲው ህወሃት በሰሜን እዝ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚዘክር መርሃ ግብር አካዷል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶችና የከተማዋ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
 
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የአባቶቻችን የድል አድራጊነት ታሪክ በእኔና በእናንተ ይደገማል እንጂ አይበላሽም፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ታሸንፋለች ነው ያሉት ።
 
የኢትዮጵያ ሰራዊትየጀግኖች ጀግና መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ÷ አይደለም አሸባሪው የህወሓት ቡድን ጁንታ በዘመናዊ መልክ የጦር መሳሪያ የታጠቁትን የመከቱና ያባረሩ የአባቶቻችን ልጆች ነን ሲሉ ተናግረዋል ።
 
መላው የከተማዋ ነዋሪዎችም ተደራጅቶ አከባቢውን በመጠበቅ ማንኛውንም አይነት የክፋት ተግባር ለጸጥታ አካላት በማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ከደጀን እስከ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊትን ጎን እንዲሰለፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው÷ ለኢትዮጵያ ሀገራችን መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጀን ሠራዊት ነን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊ በባርነት የመኖር ታሪክ የለውም ያሉትሌተናል ጀነራል ባጫ ÷ ባንዳውን እና የሽብር ቡድኑን ህወሓት በአጭር ጊዜ ለመቅበር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በቆንጅት ዘውዴ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
 
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
 
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.