Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሀገሪቱ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረክታል-የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም በሀገሪቱ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት ጉልህ ድርሻ እንዳለው የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ገለጹ።
ህብረተሰቡም ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በንቃት መጠበቅ እና ሰርጎ ገቦችን ማጋለጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በክልሉ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት እንደተናገሩት ፥መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ትክክለኛና ተገቢነት ያለው ውሳኔ ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር እንዲሁም ሀገርን ለመታደግ የተላለፈ ውሳኔ ስለመሆኑ አንስተዋል።
እንደ ነዋሪዎቹ አስተያየትም አዋጁ አሸባሪው ህውሓት ሀገር ለማፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ ለመመከት ያግዛል።
በተለይም በየአካባቢው ከአሸባሪው ህውሓት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰርጎ ገቦችን እና ባንዳዎችን ለመለየትና የጥፋት ተልዕኮን ለመከላከል እንደሚያስችል ነው የተናገሩት፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት መጠበቅና የአሸባሪው ህውሓት ተባባሪዎችን በማጋለጥ ወደ ህግ እንዲቀርቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለአዋጁ ተፈፃሚነትም የበኩላቸው እንደሚወጡ ነው ነዋሪዎቹ የገለፁት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.