Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ በመቀልበስ ለኢትዮጵያን ክብር እንቆማለን- የፖለቲካ የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳያግደን የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ ለመቀልበስ ከመንግስት ጎን ተሰልፈን ለኢትዮጵያ አንድነትና ክብር እንቆማለን ሲሉ በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አረጋገጠ።

በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አበበ ለሰልፈኛው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ከማንምና ከማንም በላይ ናት፤ የፖለቲካ ልዩነትም ከሀገር በታች ነው ብለዋል።

ከውስጣችን የወጡ ባንዳዎች ሀገራችንን ለማተራመስ የፈለጉትን ጥረት ቢያደርጉም በተባበረ ክንዳችን አሳፍረን እንመልሳቸዋለን ብለዋል የጋራ ምክር ቤቱ ስብሳቢ።

አሸባሪውን ቡድን ወደ መረጠው ሲኦል ልከን፥ የሁላችን አገር የሆነችውን ኢትዮጵያን እንገነባለን ነው ያሉት ።

ያለምንም ቅድመ ሁኔታና የፖለቲካ ልዩነት ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ ለማድረስ እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል።

ለማንም የውጭ አገር ድንፋና ማስፈራሪያ አንበረከክመ ያሉት ተወካዩ፥ የአገራችንን ክብር ለማሰጠበቅ አስፈላጊውን ዋጋ እንከፍላለን ብለዋል።

ለሉዓላዊታችን መከበር ህይወታቸውን ለሰጡ ጀግኖችና ድጋፍ ለሚያደርጉ ወገኖች ሁሉ ምስጋና እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.