Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙሃን የሚያስተላልፉት መረጃ እጅጉን የተሳሳተ ነው- ለጉብኝት የመጡ አሜሪካዊያን

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታና ዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙሃን የሚያስተላልፉት መረጃ እጅጉን የተለያየ መሆኑን አሜሪካዊያን ገለጹ።
በውጭ ሚዲያዎች ስለ ኢትዮጵያ የሚገለጸውና መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ እውነታ እጅጉን የተለየ መሆኑን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጡ አሜሪካዊያን የአሜሪካ ዜጎች ተናገሩ።
ከአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት የመጡት ሬይ ማክልስ እንደገለጹት÷ በምዕራቡ ዓለም ሚዲያ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የምትሰማውና ቦታው ላይ ተገኝተህ የምታየው ነገር መሬት ላይ ካለው እውነት ይልቅ የሚዲያው ውሸት ይገዝፋል ብለዋል።
እኔም ሆንኩ ጋደኞቼ ተዘዋውረን ባየናቸው አከባቢዎች ምንም የገጠመን ችግር የለም ያሉት ሬይ÷ የምዕራቡ ሚዲያ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ግጭት እንዳለና ሀገሪቷ ያልተረጋጋች አድርገው የሚያሰራጩት ዘገባ ተገቢነት የለውም ነው ያሉት።
 ኢትዮጵያን ላለፉት 20 ዓመታት ለመጎብኘት የተመላለሱት ሌላው አሜሪካዊ ፖል አንደርሰን በበኩላቸው ዓለም አቀፍ ሚዲያ ስለኢትዮጵያ የሚያሰራጫቸው መረጃዎ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።
ከአንድ ሬስቶራንት ቁጭ ብዬ የሲኤንኤን ዘገባ ስመለከት በጣም አስቂኝ ነው የሆነብኝ ምክንያቱም ሚዲያው በወቅቱ እያሰራጨ የነበረው መረጃ ኢትዮጵያ በግጭት ማዕበል እየተናጠች ነው ይላል፤ የት ብለህ እንድትጠይቅ ያደርግሃልም ብለዋል።
ለምን እንደሚዘግቡም ግልጽ አይደለም ያሉት አስተያየት ሰጭዎች÷ ኢትዮጵያ በሰኔ ወር 2013 ዓ. ም ላይ ያካሄደችውን ምርጫ አዲስ አበባ ከተማ በመገኘት የምርጫውን ሂደት የማየት እድል እንደነበራቸው መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.