Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና ሙሉ ዝግጅት ተደርጎ በዛሬው እለት ፈተናው መሰጠት ተጀምሯል ሲል ገልጿል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ፈተናው እንዳይስተጓጎል የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

ከፈተና ኩረጃ ጋር ተያይዞም ከስነምግባርና ፀረሙስና ጋር በመቀናጀት ግንዛቤን የማስፋት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በመሆኑም የፀጥታ ሃይሉ፣ ወላጅና አጠቃላይ ማህበረሰቡ የፈተና አሰጣጡ በሰላም እንዲጠናቀቅና ስኬታማ እንዲሆን የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ በሁለት ጣቢያዎች በሚሰጠው ፈተናም 1 ሺህ 267 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.