Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በውሸት ዘመቻ ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ትልልቅ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ዘመቻ ቢያካሂዱም ያሰቡትን ማሳካት እንዳልቻሉ አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ተቀነባብረው የሚቀርቡ በርከት ያሉ የሀሰት ዘመቻዎችን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በትኩረት በመስራት እቅዳቸውን እና አላማቸውን ማክሸፍ ይገባል ተብሏል::

ኢትዮጵያ የሰላም ጉዳይ የሁልጊዜ አጀንዳዋ መሆኑን ያነሱት ቃል አቀባዩ፥ በመንግስት በኩል ያለው እና የነበረው ፍላጎት ተመሳሳይ እንደሆነ ተናግረዋል::

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተም ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች ማብራሪያ መቅረቡ በመግለጫቸው አንስተዋል።

ከተለያዩ አገራት ተወካዮች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ አመርቂ ውይይቶች መደረጋቸውም ተገልጿል::

በአዲሱ ሙሉነህ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.