Fana: At a Speed of Life!

አለም አቀፍ አጋሮቻችን የኢትዮጵያን ህዝብ ፍላጎት ያክብሩ – ዶ/ር አብርሃም በላይ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 04 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁን ሰዓት ከ100 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያንን ለማተራመስ ከውስጥ እና ከውጭ ከፍተኛ የፀጥታ ችግር ገጥሟል ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ገለጹ ።

ሀገሪቱን ለማዳከም እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግስት ለመገልበጥ እነዚህ አጭበርባሪ ተዋናዮች የሕዝቡን ስነ -ልቦና ግምት ውስጥ ያላስገቡትን የራሳቸውን አሻንጉሊት ለማስቀመጥ ያላቸውን ፍላጎት በድፍረት አውጀዋል ብለዋል ዶ/ር አብረሃም።

ለአለም አቀፍ አጋሮቻችን የምናቀርበው ጥሪ የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን ምርጫ ለማክበር እና ለመጠበቅ እንዲሁም የአሸባሪውን የህውሀት ከፋፋይ አጀንዳ ለመፋለም የኢትዮጵያ መንግስት ጥረትን ተረድተው እንዲደግፉ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሀገራችን እና ለመላው ዜጎቿ ደህንነት መጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በአገራችን ውስጥ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እየሰሩ ንፁሀን የትግራይ ተወላጆችን በውሸት እየወነጀሉ፣ አጸፋውን እንዲመልሱላቸው እና የሽብርተኝነት አጀንዳቸውን ለማስፈጸም የሚሰሩም አሉ ብለዋል።

የሀገራችንን ቀውስ ለማባባስ እና ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ሌሎች ተዋናዮችም ያሉ ሲሆን ይህንንም ለመፍታት ከፌዴራል ፖሊስና በሌሎች ተቋማት የተከናወኑ ተግባራትን እና የአሰራር ሂደቶችን የሚገመግም ኮሚቴ አቋቁመን የስነ ምግባር ጉድለት ሲያጋጥም ለማወቅና ተሳታፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

የትግራይ ጉዳይ ግድ ከሚላቸው አካላት ጋር በመሆን ንፁሀን እንዲጠበቁ ለመርዳት አሰራሮችን ለመፈተሽ እና ለመገምገም እና ንፁሀን እንዲጠበቁ እየሰራን ነው ነው ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ በፈተና ጊዜ፣ አንዳንድ ስህተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ እንገነዘባለን ሆኖም ሁሉም ጉዳዩች በህግ አግባብ እንዲፈጸሙ ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።

አንድነታችን ጥንካሬያችን ነው። በምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ለሉዓላዊነትና ሰላም ይረጋገጣል ፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እኛን ለመርዳት ጥረት ለሚያደርጉ ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.