Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ሙከራ ቅዠት ሆኗል – ዶ/ር አለሙ ስሜ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ሙከራ በአፋር ልጆች ተጋድሎ ቅዠት ሆኖ ቀርቶበታል ሲሉ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር አለሙ ስሜ ገለጹ።
በአፋር ክልል የፈንቲረሱ ዞን ወጣቶች በፈጠሩት ጠንካራ አደረጃጀት የሽብር ቡድኑን ታጣቂዎች መግቢያ መውጫ አሳጥቷቸዋል።
የአካባቢው ወጣቶች እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያዊነትን ከአፋር ልብ ፍቆ ማውጣት ባይችልም ባይተዋር አድርጎት ቆይቷል ብለዋል።
ወጣቶቹ ክህደት የማይሰለቸውን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ ቀን ከሌሊት ነቅተን እየጠበቅን ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ህወሃት በአገዛዝ ዘመኑ የአፋርን የኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና ለመሸርሸር መስራቱን አስታውሷል።
አፋር በአገሩ ድርድር አያውቅም ያሉት ወጣቶቹ÷ ስለሆነም ቡድኑ ከገባበት ቦታ እንዳይወጣ ተደርጎ መቀበር አለበት ብለዋል፡፡
ይሄን አገርን ሊደፍር የመጣን ነውረኛ ቡድን በገባበት መቅበር ይገባል፤ አፋር ገብተን ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብሎ የገባው ሽፍታ÷ በመጀመሪያ ደረጃ አይገባም ከገባም ባዘጋጀንለት ጉድጓድ ይቀበራል ሲሉ ገልጸዋል።
በአፋር ክልል የፈንቲረሱ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ሀላፊ አቶ መሀመድ የሴጌሌ÷ ጠላት በገባባቸው የአፋር ክልል አካባቢዎች መውጫ አጥቶ እየተቀጠቀጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ሊሆን የቻለው የአፋር ህዝብ ጠንካራ አደረጃጀት ፈጥሮ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ በመቻሉ እንደሆነ አመልክተዋል።
የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ ክልሉ በሚያደርገው ብርቱ ተጋድሎ የፌዴራል መንግስትና የአማራ ክልል ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶ/ር አለሙ ስሜ÷ ለሀገር ክብርና ሉዓላዊነት መቆምን ከአፋር ህዝብ ታላቅ ገድል መማር አለብን ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ በአፋር በኩል የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በእንቁዎቹ የአፋር ልጆች መክኖበታል፣ ፍላጎቱም ቅዠት ሆኖ ቀርቶበታል ብለዋል።
አሸባሪው ቡድኑ ከተቀበረበት ጎሬ በወጣ ቁጥር ሞቱን እያፋጠነ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አለሙ÷ በአፋርና አማራ ክልሎች ቡድኑ የደረሰበት ኪሳራ ጥሩ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያውያን ያሳየነው ትብብር አሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን ብቻ ሳይሆን÷ የእኛን መሪ መሾም መሻር የሚፈልጉ የሩቅ ጠላቶችም ከነኩን የማንመለስ የእሳት አሎሎ መሆናችን ማሳያ ነው ብለዋል።
በአገራቸው ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣን ጥቃት የማይታገሱት የአፋር ጀግኖችን ለመደገፍ የፌዴራል መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.