Fana: At a Speed of Life!

ለህልውና ዘመቻው 2ኛ ዙር ድጋፍ ለማድረግ ወደ ተግባር መግባቱን ኮሚቴው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህልውና ዘመቻው በግንባር እየታገሉ ላሉ የጸታ አካላት በሁለተኛ ዙር ድጋፍ ከ 5 ሚሊየን 286 ሺህ ብር በላይ ለመሰብሰብ ወደተግባር መግባቱን የመተከል ዞን ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ።
የገቢ አሰባሰቡ መርሃ ግብር ‹‹በተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ የኢትዮጵያን አሸናፊነት እናረጋግጣለን›› በሚል መሪቃል ከጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ ከመተከል ኮሙኒኬሽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ድርጅቶችና የመንግስት ተቋማት በማሳተፍ ገቢ ለማሰባሰብ ሁሉም ወረዳዎች የድርሻቸውን በማበርከት ለሰራዊቱ ደጀንነታቸውን ማሳየት ይገባል ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አቢዮት አልቦሮ አሳስበዋል።
በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ላይ ሁሉም የአቅሙን እንዲወጣ የግንዛቤ ስራዎች እንደሚሰራ ጠቁመው÷ ይህ ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊው ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግም የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ተናግረዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.