Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ህዝብ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ 5ሺህ 100 ሰንጋዎችን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎች አደረገ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዕርስቱ ይርዳዉ ÷ የክልሉ ህዝብ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ 5100 ሰንጋዎችን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ከሰንጋዎች በተጨማሪ ለመከላከያ ሰራዊቱ ስንቅ የሚሆኑም በእናቶች ተዘጋጅቶ ድጋፍ ተደርጓል ነዉ ያሉት።

የተደረገው ድጋፍ ወደ 380 ሚሊየን ብር እንደሚገመትም ነዉ የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እስኪከበር ድረስ የክልሉ መንግስት ድጋፉን አጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ድጋፉን የመከላከያ ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ ማርታ ላዉጂ ተረክበዋል።

በቢቂላ ቱፋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.