Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቅንጅት የፈጠሩ አካላት በተባበረ ክንዳችን ይፈርሳሉ-ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 05፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቅንጅ የፈጠሩት አካላት በተባበረ ክንዳችን ይፈርሳሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
 
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ዛሬ እንኳን ህዝቡ ምድሩ ሳይቀር ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እየተዋጋ ባለበት የጀግኖች መገኛ ምድር አፋር ተገኝተናል ብለዋል፡፡
 
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የኢትዮጵያ ከብረት የጠነከረ ምሽግ፣ እንኳን ሕዝቡ ግመሎቹ እንኳን በኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩት፣በታሪኩ የባንዳነት ሳይሆን የጀግንነት የሆነው የአፋር ህዝብ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ ሊጥል የመጣ የትኛውም ወራሪ በአፋር ምድር ትቢያ ሆኖ እንዲቀር እያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
 
አሸባሪዉ ጁንታ የእናት ጡት ነካሽ ያሰበው ሁሉ አልሳካ ሲለው ህፃናትን ፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞችን በተኙበት በከባድ መሳሪያ ሳይቀር በመደብደብ የፈሪ በትሩን ፋሽስታዊ ግፉን መፈጸሙንም አንስተዋል፡፡
 
አሁን ላይም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የአፋር ልዩ ሃይሎች እየተከታተሉ የእጁን እየሰጡት ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 16 ሚሊየን ብር ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ አይነት ድጋፎችን በረሃው ጉልበት ሆኖት በአፋር ግምባር ለሚገኘዉና በድል ላይ ድል እያስመዘገበ ላለው ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና ለአፋር ልዩ ሀይሎች በሰመራና በአዋሽ ሰባት በመገኘት ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡
 
በርክክብ ስነ ስርዓቱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና ሱልጣኖች መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡
 
በአፋር ምድር ህዝቡ ብቻ ሳይሆን አየሩ ጭምር ወራሪውን ድል እየነሳው ይገኛል፤ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ የተባበሩትን በተባበረ ክንዳችን ይፈርሳሉም ብለዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.