Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉሙሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል÷ 26 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 3 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በ11 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ጅግጅጋ፣ ሞያሌ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚ ሲሆኑ÷ በቅደም ተከተላቸውም 10 ነጥብ 6፣ 4 ነጥብ 8 እና 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ መያዛቸውም ተገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጸች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል መባሉን ከጉሙሩክ ኮሚሽን ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ÷ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ኅብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.