Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል በሰሜኑ ግጭት ጣልቃ እንዲገባም ሆነ ሃይል ሊያሰፍር አይገባም – የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለአሜሪካ መንግስት ግልፅ መልእክት ማስተላለፍ የምንፈልገው የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል በሰሜኑ ግጭት ጣልቃ እንዲገባም ሆነ ሃይል ሊያሰፍር አይገባም “ ሲል የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት አስገነዘበ።

ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ለአሜሪካን ኮንግረስ፣ ለአሜሪካ ውጪጉዳይ እና ለአሜሪካን መከላከያ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እንደማይገባ አስገንዝቧል።

በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የመከላከያ መሪዎች በኢትዮጵያ ባለው የሰሜኑ ግጭት አሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ልታካሂድ ትችላለች ማለታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ሊቀ መንበርና ተባባሪ መስራች ዲያቆን ዮሴፍ መግለጫ አውጥተዋል።

“ለአሜሪካ መንግስት ግልፅ መልእክት ማስተላለፍ የምንፈልገው የአሜሪካ ወታደራዊ ሃይል በሰሜኑ ግጭት ጣልቃ እንዲገባም ሆነ ሃይል ሊያሰፍር አይገባም “ ብለዋል በመግለጫቸው።

በትግራይ ያለው ግጭት የውስጥ ጉዳይ ሆኖ በኢትዮጵያውያን እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጠው መንግስታቸው ብቻ ሊያዝ እንደሚገባም አመላክተዋል።

“ኢትዮጵያ አሜሪካውያንን ወክለን እንደምንናገረው የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ከማባባስ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን” ያለው መግለጫው የአሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ሃላፊነት የጎደለውና የተሳሳተ ውሳኔ ነው።

ይህም አሜሪካ ለ20 አመታት በአፍጋኒስታን በነበራት ቆይታ በመጨረሻዎቹ አመታት ተፈጥሮ የነበረውን ቀውስ ማንም የሚያስታውሰው ነው አብዛኞቹ አሜሪካውያንም ይህን ድርጊት ተቃውመውታል።

የአሜሪካ መንግስት ይልቁንም የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ እንዲተገብር ምክር ቤቱ ጠይቋል።

ሚዛናዊ የሆነ አቀራረብ በሌለበት ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷን ከማይጋፉ ሃይሎች ጋር ጥምረት ለመፍጠር ትገደዳለች፤ በኢትዮጵያ የሚደረግ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ለማያባራ ቀጣናዊ የፖለቲካዊ ቀውስ ይዳርጋል ይህም ቀጣናውና የአለም ደህንነትን በማናጋት ጭምር ቀውሱን ያባብሳል።

ምክር ቤቱ የኢትጵያና የአሜሪካውያን ወታደራዊ ጥምረት ለብሄራዊ ደህንነት ያለውን ፋይዳ ይረዳል እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያላቸውን ፋይዳ ይገነዘባል፤ በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዜጎች ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት የከፈሉትን ዋጋም ማንሳት አስፈላጊ ነው።

አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተሰሚነት ለማስቀጠል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን 118 አመታት ያስቆጠረ ግንኙነት ዳግም የምታጤንበት ወቅት መሆኑን የጠቆመው ምክር ቤቱ፤ ይህን አላማ ማስቀጠል የሚቻለውም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን በመከባበርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ በማተኮር እንደሆነ አመልክቷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
A
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.