Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአዲስ አበባ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በመሆን ከተማዋን አጽድተዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር በመሆን በመዲናዋ የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

የጽዳት ዘመቻው “ቆሻሻ አስተሳሰብን እና ቆሻሻን ከከተማዬ አጸዳለሁ” በሚል መሪ ቃል ነው በዛሬው እለት የተካሄደው።

በዘመቻው ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የተከማዋ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በዛሬው እለት በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ እና ችግኝ መንከባከብ መርሃግብር መካሄዱን ነው የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያስታወቀው።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ላለፉት ቀናት ስልጠና ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.