Fana: At a Speed of Life!

ሀይቅ፣ ቢስቲማና ለሚ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠባቸው ቀሪ ከተሞች በድጋሚ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተደረገ ባለው ርብርብ በደብረ ብርሀን ዲስትሪክት ስር የሚገኘው ለሚ ከተማ እንዲሁም በደሴ ዲስትሪክት ስር የሚገኙት ሀይቅና ቢስቲማ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል በዛሬው ዕለት አግኝተዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ ማሰራጫ እና ማስተላለፊያ መስመሮች በመጠገን ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን ኃይል መልሰው እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በዚህም ከተሞች ነፃ በወጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ በደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ስር ያሉ ሁሉም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ በደሴ ዲስትሪከት ስር ከሚገኙ 23 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መካከል ከጋሸና ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ከሚያገኘው ወገል ጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከልና ከወልድያ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ከሚያገኘው ውጫሌ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በስተቀር በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ ሌሎች 21 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት መቻላቸውን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.