Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎው በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች 1 ሺህ 500 እና 800 ሜትር ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች። በሻምፒዮናው በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ፍሬወይኒ ሀይሉ 4:01.46 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች። በተመሳሳይ በሻምፒዮናው የሴቶች 800 ሜትር ውድድር ጽጌ ዱጉማ 2:01.90 በሆነ ሰዓት በመግባት የወርቅ ሜዳልያ አምጥታለች።
Read More...

ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አብዱልከሪም ወርቁ፣ ብሩክ በየነ እና ጊት ጋትኩት(በራስ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡ የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዳማ ከተማ በድሬዳዋ…

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። ትናንት ምሽት በተካሄደው የሴቶች 3 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ጉዳፍ ፀጋዬ በ8:21.13 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በማጠናቀቅ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ ለምለም ሀይሉ በ8:30.36…

ሊቨርፑል እና ቶተንሃም ተገጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የ27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሊቨርፑል፣ ቶተንሃምና ኒውካስል ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ቼልሲ አቻ ተለያይቷል፡፡ ምሽት 12፡00 ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ቶተንሃም ክርስታል ፓላስን 3 ለ 1፣ ሊቨርፑል ኖቲንግሃም ፎረስትን 1 ለ 0 እንዲሁም ኒውካስል ዎልቭስን 3 ለ 0…

በ800 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ የተሳተፉ ሁለቱም አትሌቶች ለነገው የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል።   ከምድብ አንድ አትሌት ፅጌ ድጉማ በ1 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ ከ38 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ ውድድሩን በቀዳሚነት…

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማጣሪያውን አለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎ እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተወዳደሩባቸው የተለያዩ እርቀቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት÷ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴት ማጣሪያ ከምድብ አንድ ፍሬወይኒ ኃይሉ 1ኛ፣ ከምድብ ሦስት ድርቤ ወልተጂ 1ኛ እንዲሁም ከምድብ አራት ብርቄ ኃየሎም 2ኛ…

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማጣሪያውን በቀዳሚነት አለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የ800 ሜትር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያየ ምድብ ማጣሪያውን አልፈዋል፡፡ ከምድብ አንድ አትሌት ሀብታም ዓለሙ እንዲሁም ከምድብ አራት ጽጌ ዱጉማ 2 ደቂቃ ከ50 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡ በሌላ በኩል ምሽት…