Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ማጣሪያውን አለፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በግላስጎ እየተካሄደ በሚገኘው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተወዳደሩባቸው የተለያዩ እርቀቶች ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል፡፡

በዚሁ መሠረት÷ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴት ማጣሪያ ከምድብ አንድ ፍሬወይኒ ኃይሉ 1ኛ፣ ከምድብ ሦስት ድርቤ ወልተጂ 1ኛ እንዲሁም ከምድብ አራት ብርቄ ኃየሎም 2ኛ በመውጣት ወደቀጣዩ ውድድር አልፈዋል።

በተመሳሳይ እርቅት በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ÷ ከምድብ አንድ ሳሙኤል ተፈራ 3ኛ በመውጣት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ እርቀት ከምድብ ሦስት ተወዳድሮ 6ኛ የወጣው ቢኒያም መሃሪ ሲጨርስ ተገፍቶ ወድቆ ወደኋላ ቢቀርም ለመጨረስ ባደረገው ጥረት በዳኛ ውሳኔ ወደ ለፍፃሜ ውድድር ማለፍ ችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.