Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው፡፡ በርካታ ታዳጊ አትሌቶች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከታህሳስ 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በአሎሎ ውርወራ፣ በዲስከስስ ውርወራ፣ በ400 ሜትር ሴቶችና ወንዶች በ800 ሜትር ሴቶችና ወንዶች የፍጻሜ ውድድርና በርከት ያሉ የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡ የሁለተኛ ቀን የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ከ16…
Read More...

የአዲስ አበባ የብሄራዊ ስታዲየም ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስራው ከ4 ዓመት በፊት የተጀመረው በኢትዮጵያ ግዙፍ የተባለውና በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው ብሄራዊ ስታዲየም የመጀመሪያው ምእራፍ የግንባታ ተጠናቆ፤ ሁለተኛ ምእራፍ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀምር ተገለፀ።   በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በቻይናው ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ እየተገነባ ያለው ስታዲየም…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ መቐለ ላይ ተካሂዷል። በትግራይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። ለመቐለ 70 እንደርታ አማኑኤል ገብረሚካኤል የማሸነፊያ ጎሏን አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎም ወልዋሎና መቐለ 70 እንደርታ ሊጉን…

ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያ የንቅናቄና ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልል ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ እስከ ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን፥ በየደረጃዉ የሚገኙ የስፖርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል። በሀገራዊ የስፖርት ማሻሻያው ላይ በአዳማ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ስፖርት…

የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሞተር ስፖርት ውድድር ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ።   ማህበሩ በሁለት ዙር 60 ታዳጊ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 46ቱን ለምረቃ አብቅቷል።   ከተመራቂዎቹ መካከል አስሩ…

በፕሪምየር ሊጉ ወልቂጤ ፣ ጅማ አባ ጅፋርና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት በዛሬው ዕለት ስድስት ጨዋታዎችን በክልል ከተማዎች አስተናግዷል፡፡ በዚህም ወደ ጅማ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ በጅማ አባ ጅፋር 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡ የጅማ አባ ጅፋርን የማሸነፊያ ግቦች ብዙዓየሁ እንደሻው በ13ኛው ደቂቃ እና አምረላ ደልታታ በ80ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥሩ…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 6 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሰ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ቀጥለው ይካሄዳሉ። በዛሬው እለት ስድስት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፥ ሁሉም ጨዋታዎች በክልል ከተሞች የሚደረጉ ይሆናል። በዚህም ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ ስሹል ሽረ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ። ከዚህ ባለፈም…