Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ከዓለም አራተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢስ) በኬኒያ ናይሮቢ ሲካሄድ በቆየው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከዓለም አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ በውድድሩ ኢትዮጵያ ሶስት ወርቅ፣ ሰባት ብር እና ሁለት የነሃስ በድምሩ አስራ ሁለት ሜዳልያዎችን አግኝታለች፡፡ በዚህም ኬንያን፣ ፊንላንድንና ናይጄሪያን ተከትላ ከዓለም አራተኛ ደረጃን በመያዝ ሻምፒዮናውን ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ …
Read More...

አትሌት ሚዛን አለም ለኢትዮጵያ ሦስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በመጨረሻው ቀን ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች በተለያየ መርሃግብር ተሳትፈዋል፡፡ በ5000 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሚዛን አለም በ16:05.61 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ…

በተለያዩ አካባቢዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን የሚገልጽ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ አካባቢዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን የሚገልጽ የድጋፍ ሰልፍና የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል። በአዲስ አበባ ፣በጋምቤላ ፣ በአሶሳ ፣ በወልቂጤ፣ በሀረሪ፣ በሀላባ እና በሌሎች ከተሞች ለመከላከያ የድጋፍ ሰልፍ እና የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ተካሂዷል። በሀላባ ከተማ " እኔም…

በሀረር ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን ለመግለጽ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) "የትም፣ መቼም፣ በምንም ለኢትዮዽያ እዘምታለው" በሚል መሪ ሀሳብ በሐረር ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ። ለጀግናው የአገር መከላከያ አጋርነትን የመግለጽ ዓላማ ባለው በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ የክልሉ ነዋሪዎች፣ አትሌቶችና በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ተሳትፈዋል።…

የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል። በዛሬው ዕለት በሚካሄደው የመዝጊያ ውድድር ላይም ኢትዮጵያ በ800 ሜ ወንዶች ፣ በ1500 ሜ ሴቶች ፣ 3000 ሜ መሰናክል ወንዶች ፣5000 ሜ ሴቶች፣ 4 X…

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች አትሌት አያል የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት አያል ዳኛቸው የወርቅ ሜዳልያ አሸነፈች፡፡ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር ለኢትዮጵያ ሁለተኛው የወርቅ ሜዳልያ በመሆን ተመዝግቧል፡፡ አትሌት አያል ዳኛቸው…

ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ነሐሴ 28 ያከናውናሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን የሚያደርግባቸው ቀናት ታውቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 7 ከጋና፣ዚምቧቡዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር መደልደሉ ይታወቃል። ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን…