Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ በደረሠ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በመምሪያው የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አደጋው የደረሰው ከባሶ ሊበን ወረዳ ወደ አዋበል ወረዳ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ተኩል አካባቢ አነደድ ወረዳ ልዩ ቦታው ወንጋ ንፋሳም ቀበሌ ሲደርስ በመገልበጡ ምክንያት 9 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ በ20 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።
አሽከርካሪው አለመያዙ የታወቀ ሲሆን ፖሊስ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

አደጋው የደረሰበት አካባቢ ቁልቁለትና ጠመዝማዛ መንገድ ሲሆን የአደጋው መንስዔ እየተጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሰላም አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.