Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ለኢጋድ እና የአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮች በህግ ማስከበር ዘመቻው ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን መቀመጫቸውን አንካራ ላደረጉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነት መንግስታት (ኢጋድ) እና የአፍሪካ አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ስለተወሰደው ህግ ማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ።

አምባሳደር ግርማ ተመስገን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት በቱርክ ለሚገኙ የአውሮፓ እና እስያ የሚሲዮን መሪዎችም ማብሪያ ተሰጥቷል።

በማብራሪያቸውም መንግሥት ህግ የማስክበር ዘመቻውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ፊቱን የሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብና በአፈንጋጩ ኃይል የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የማቋቋም ስራ እየሰራ መሆኑን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም በማድረግ ወደ ስራ እንዲገባ ማድረጉንም ለአምባሳደሮቹ ገልጸውላቸዋል፡፡

ሕግን የማስከበር እርምጃው በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን እንደተዘገበው ሳይሆን የጁንታውን ቡድን ለህግ የማቅረብና ህግና ስርአትን የማስከበር እንደነበርም በማብራሪያቸው አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር ግርማ መንግሥት ሕግን ለማስከበር በወሰዳቸው እርምጃዎች የአፍሪካ ሕብረት እና ጎረቤት የኢጋድ አባል ሀገራት ላደረጉትአስተዋጽኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቱርክ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከአሁን በፊት ለቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ለተለያዩ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሲሰጥ ቆይቷል።

በአምስት የተለያዩ የቱርክ ከተሞች (ኢዝሚር፣ ኮንያ፣ አዳና፣ ቡርሳና መርሲን) እንዲሁም አዘርባጃን ባኩ ከሚገኙ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስላዎች ጋር በመተባበር በእነዚህ ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት ኃላፊዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉም ተገልጿል፡፡

በስላባት ማናዬ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.