Fana: At a Speed of Life!

በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል ተቋቋመ።

በሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው እና አቶ ሃይላይ ብርሃነ የተመራ የልዑካን ቡድን በአማራ ክልል አዊ ዞን በቻግኒ ከተማ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በደረሰው ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከል አቋቁሟል።

በቻግኒ ከተማ የማስተባበሪያ ማዕከሉን ስራ በይፋ ያስጀመረው የልዑካን ቡድን ትኩረት የሚያሻቸው ጉዳዮች ለይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

ተፈናቃዮች የሚያስፈልጋቸውን አስቸኳይ ድጋፍ መለየት፤ የደረሰውን ጉዳት ዓይነትና መጠን መለየት፤ ከሰብዓዊ ድጋፍ ስራ ባሻገር ተፈናቃዮችም ሆኑ ነዋሪዎች ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይገጥማቸው ደህንነታቸውን ማረጋገጥ፤ የፀጥታ አካሉን ቁርጠኝነት ማረጋገጥ፤  ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት ካሉ ማረጋገጥና ለወደፊት እጣፈንታቸውን መወሰን እንዲቻል በአፋጣኝ መለየት፤ ተፈናቃይ ሆነው ይበልጥ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት፣ ነብሰጡር ሴቶች፣ የሚያጠቡ እናቶች እና አቅመ ደካሞችን ቅድሚያ በመስጠት ሰብዓዊ ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያገኙ ማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከሉ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚሆኑ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል ፡፡

የማዕከሉ ዋና አላማ ፈጣን ምላሽ መስጠት ሲሆን ለተፈናቃዮችና ለተጠቂዎች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ መስጠት ነው ተብሏል፡፡

ቀጠዩ እርምጃ የሁኔታ ዳሰሳ በማድረግ ተጎጂ ወገኖችን አወያይቶ ወደቀያቸው የመመለስ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት መሆኑም ተገልጿል፡፡

ህግ ማስከበርና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብም ቀዳሚ ተግባር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የቻግኒ ከተማ አስተዳደርም የአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት ማስተባበሪያ ማዕከሉ አባል በመሆኑ በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከተሰማሩ ባለ ብዙ ዘርፍ የባለሙያ ቡድኖች ጋር በመናበብ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በጊዜያዊ የመጠለያ ካምፖች በመገኘት ተጎጂዎችን በማነጋገር ጠቃሚ መረጃዎችን ሰብስቦ ለአስቸኳይ ጊዜ ተግባራት አስተባባሪ ማዕከሉ የስራ መመሪያ መስጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.