Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ምሁራን ተናገሩ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሁራን በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ተናገሩ።

ምሁራንና የዘርፉ ባለሙያዎች ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን ጨምሮ የልማት ተነሺ ተወካዮች ተገኝተው የጋራ አቋም ለመያዝ የሚረዳ የፓናል ውይይት አድርገዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ ዓለም አቀፍ የከተሞችን ደረጃ የማሻሻል ተሞክሮዎችን ዋቢ በማድረግ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል።

በፓናል ውይይቱ የተገኙት የሲቪል ሙያዎችና የከተማ ማደስ የዕቅድ ስራዎች ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ሂርጶ በሬሳ÷ በታዳጊ አገራት የከተሞችን ገቢ ለማሳደግ ፤የመሰረተ ልማት ዝርጋታን ለማሻሻል፤ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፤የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስፋትና የቅርሶች ይዞታ ለማሻሻል የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የኮምፓስ የማማከር አገልግሎት ድርጅት ዋና ስ/አስፈፃሚ አቶ ጎሳዬ በቀለ በበኩላቸው÷ የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በበቂ ጥናት ተግባራዊ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ወደ ፊት በሚኖረው ውጤትም በኢኮኖሚ፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ ውስን የመሬት ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ ሞገስ ጥበቡ (ኢ/ር) ÷ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች በሚፈለገው ፍጥነትና የጥራት ልክ ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.