Fana: At a Speed of Life!

በወራቤ ከተማ የእሳት አደጋ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በወራቤ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ዱና ስታዲየም ፊት ለፊት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት ገደማ ድንገት በተነሳ የእሳት አደጋ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት ሲደርስ አራት ቤቶች ተቃጥለዋል።

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን አብዱረሂም ሁሴን እንደገለጹት በእሳት አደጋው በአንድ ሰው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን÷ የአደጋው ተጎጂ በህክምና ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በከተማው የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስዔ በመጣራት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

እንደ ዋና ሳጅን ሁሴን ገለጻ ህብረተሰቡ እንደ ቤንዚን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን በመኖሪያ አካባቢ ማኖር የለበትም ሲሉም አስገንዝበዋል።

የእሳት ቃጠሎው በከተማው የእሳት አደጋ ተሽከርካሪ እና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን÷ የደረሰው የአደጋ መጠን በመጣራት ላይ መሆኑን ማስረዳታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.