Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ አዋሳኝ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ እንዳይስፋፋ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንበጣ መንጋ የወረባቦ ወረዳን በሚያዋስነው የአፋር ክልል የጭፍራ ወረዳ መከሰቱን የወረባቦ ወረዳ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሙአዝ መሀመድ አስታወቁ፡፡
የአንበጣ መንጋ ው የአፋር አዋሳኝ ወደሆኑት የደቡብ ወሎ አካባቢዎች በተለይም ወደ ወረባቦ ከመግባቱ በፊት ባለበት እንዲጠፋ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባም ነው ምክትል ኃላፊው ያሳሰቡት፡፡
መንጋው ጉዳት ከማድረሱ በፊት ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ምክትል ኃላፊው መንጋው ወደ አካባቢው እንዳይገባ ከፌደራል መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ አርሶ አደሩ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አሊ ሠይድ በበኩላቸው÷ በአፋር ክልል በኩል የአንበጣ መንጋ ስጋት እንዳለ ገልጸው÷ የመምሪያው ቡድን ወደ አከባቢው በመጓዝ ያለውን ስጋት በመመልከት መሰራት ያለበትን ተግባር ለመወሰን እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
መምሪያው ችግሩን ለመመልከት ወደ ቦታው እንደሚጓዝ ጠቁመው÷ የአንበጣ መንጋው እንዳይስፋፋ ለመከላከል የሚመለከተው አካል ዝግጁ እዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.