Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በኮምቦልቻ ከተማ ሐረጎ መንገድ ጋሌሳ 011 ቀበሌ ከኮምቦልቻ ከተማ ወደ ወልድያ መስመር ሲጓዝ ሚኒባስ መኪና በተመሳሳይ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ተሸከርካሪ ጋር ተጋጭተው ሚኒባሱ በግምት 150 ሜትር ጥልቀት ያለው ገደል ውስጥ ገብቷል፡፡

በውስጡም ሹፌርና ረዳቱን ጨምሮ 14 ሰው የጫነ ሲሆን በአደጋው የ3 ሰው ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን 10 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአሁኑ ወቅትም በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን አንድ ሰው ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉ ነው የተነገረው፡፡

በተጨማሪም አንድ ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን የአደጋውን መንስኤ እየተጣራ ነው፡፡

በይክበር አለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.