Fana: At a Speed of Life!

በገጠር የበይነ-መረብ ግንኙነትንለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና “ኢንተርኔት ሶሳይቲ” በገጠር የበይነ-መረብ ግንኙነትን (ኢንተርኔት) ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የተጀመረውን ስራ የሚደግፍ፣ በገጠር ጠንካራ የበይነ መረብ ግንኙነትን ለማዳረስ፣ የበይነ መረብ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የበይነ መረብ አስተዳደርን ለማሳደግ የሚያስችል ነው።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ እና የኢንተርኔት ሶሳይቲ የአፍሪካ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳዊት በቀለ ፈርመውታል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ÷አካታች ብልፅግናን ማረጋግጥን ግቡ አድርጎ የተዘጋጀው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እውን እንዲሆን መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የልማት ድርጅቶችና ማህበራት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ስትራቴጂው መሰረተ ልማቶችን ማሟላት፣ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ማልማት እና ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታን መፍጠር የሚሉትን ስለማካተቱም አብራርተዋል።

ስምምነቱ ይህንን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚደረገውን ጥረት ይደግፋልም ነው ያሉት ።

የኢንተርኔት ሶሳይቲ የአፍሪካ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳዊት በቀለ  በበኩላቸው÷ስምምነቱ  የገጠር የበይነ መረብ ግንኙነትን በማሳደግ በገጠር ያለ ሁሉም ማህበረሰብ በዲጂታል ለውጥ ውስጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል።

የኢንተርኔት ሶሳይቲ የዲጂታል የኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራን ለመደግፍ ቁርጠኛ መሆኑም አረጋግጠዋል።

ስምምነቱ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ቅድሚያ የተሰጣቸውን የግብርና፣ የማምረቻ፣ የአገልግሎትና ቱሪዝም ዘርፍን ለመደገፍ ያግዛል  ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.