ተቋማቱ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የኮንስትራክሽን ግብአት የሆኑ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ለማምረትና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በተቋማቱ መካከል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን ተናግረዋል።
ለግንባታው ዘርፍ አስፈላጊ የሆኑ እና ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሀብት መጠንን ከመለየት ጀምሮ በተገቢው ጥራት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በትብብር እንሰራለን ሲሉም ገልፀዋል።
የግንባታ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻል ለግንባታ ዘርፉ ከፍተኛ ጫናዎችን የሚያቀል እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙም የጎላ መሆኑን አስታውቀዋል።