Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ከውጭ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ሶስት የመንግስት ተቋማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር፣ ማዕድን ሚኒስቴር እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ናቸው።
ስምምነቱን የከተማና መሠረተልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ተፈራርመዋል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የኮንስትራክሽን ግብአት የሆኑ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ለማምረትና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ   በተቋማቱ መካከል የመግባቢያ ስምምነት  መፈረሙን ተናግረዋል።

 

ለግንባታው ዘርፍ አስፈላጊ የሆኑ እና ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚገቡ ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሀብት መጠንን ከመለየት ጀምሮ በተገቢው ጥራት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ በትብብር እንሰራለን ሲሉም ገልፀዋል።

 

የግንባታ ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻል ለግንባታ ዘርፉ ከፍተኛ ጫናዎችን የሚያቀል እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙም የጎላ  መሆኑን  አስታውቀዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.