Fana: At a Speed of Life!

አርሜኒያ  የተቆጣጠረችውን ቦታ አሳልፋ የሰጠችበትን ፊርማ ከአዘርባጅን ጋር ተፈራረመች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን እና ሩሲያ በአወዛጋቢው የናጎርኖ ካራባህ ግዛት ያለውን ጦርነት ለመቋጨት  ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በአዘርባጃን እና በአርሜንያ የዘር ሀረግ ባላቸው የናጎርኖ ካራባህ ታጣቂዎች መካከል ላለፉት ስድስት ሳምንታት ከባድ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ የመጣ ነው።

የአርሜኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን ስምምነቱ ለእኔም ሆነ ለሀገሬ ህዝቦች ከፍተኛ ህመም የፈጠረ ነው ብለውታል።

ስምምነቱ  የአዘርባጅን ጦር ሁኔታ  ጥልቅ ትንተና ተሰርቦት  እና በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች ውይይት አድርገውበት የተፈረመ መሆኑን ተናግረዋል።

የናጎርኖ ካራብህ ግዛት ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው የአዘርባጅን ግዛት ቢሆንም ከፈረንጆቹ 1994 ጀምሮ በአርሜኒያ የዘር ሀረግ ባላቸው ታጣቂዎች ሲተዳደር ቆይቷል።

ሀገራቱ በወቅቱ ጦርነቱን ለማቆም ተፈራርመው የነበረ ሲሆን የሰላም ስምምነት ላይ ግን አልደረሱም ነበር።

በስምምነቱ መሰረት ከ1994 ጀምሮ በአርሜያ ቁጥጥር ስር የነበረውን የናጎርኖ ካራባህ ግዛት አዘርባጅን የምትረከብ ይሆናል።

በተመሳሳይ በቀጣዩ ሳምንታት  በዚህ ግዛት አቅራቢያ ከሚገኙ አካባቢዎች ወታደሮቿን እንደምታስወጣ ነው የተነገረው።

ይህንን ተከትሎ ሩሲያ 1 ሺህ 960 ሰላም አስከባሪዎች  እንደምታሰማራ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን አስታውቀዋል።

እንዲሁም በዚህ በአካባቢው በሚደረገው የሰላም ማስከበር ስራ ቱርክ የሯሷ ሚና እንደሚኖራትም አዘርባጃን አስታውቃለች።

አርሜኒያውያንም በሀገራቱ መከካል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፋ ማድረጋቸውን ነው ቢቢሲ የዘገበው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.