Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ሁለተኛውን ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ ሁለተኛውን ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት ከአሜሪካ ፍሎሪዳ ኬኔዲ የጠፈር ማዕከል በተሳካ ሁኔታ ማምጠቋን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ አያይዞም የመጠቀው የስለላ ሳተላይት በ45 ደቂቃ ውስጥ ወደ ምህዋሩ መድረሱን ጠቁሟል፡፡

ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያን እንቅስቃሴ በሚገባ ለመቆጣጠር እስከ ፈረንጆቹ 2025 አምስት የስለላ ሳተላይቶችን ለማምጥቅ በያዘችው ዕቅድ መሰረት ይህ ሁለተኛው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር የመጀመሪያውን ሳተላይት ያመጠቀችው ደቡብ ኮሪያ ሳተላይቱ የተገጠሙለት ኤሌክትሮ ኦፕቲካል እና ኢንፍራሬድ ሴንሰሮች ከምድር አካል ላይ ግልፅ ፎቶ ማንሳት እንዳስቻሉት ተገልጿል፡፡

ሁለተኛው ሳተላይት ደግሞ ረቂቅ ሞገዶችን በመጠቀም እንደ አየሩ ሁኔታ ከምድር ጠቃሚ መረጃዎችን መሰብሰብ የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቀሪ ሦስት ሳተላይቶችም በተመሳሳይ ቴክኖሎጂ የተደራጁ እንደሚሆኑም መጠቆሙን ኤዢያ ኒውስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.