Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጂቡቲ በመንገድ፣ በባቡር መሰረተ ልማትና በወደብ አገልግሎት ያላቸውን ትብብር የማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጂቡቲ በመንገድ፣ በባቡር መሰረተ ልማትና በወደብ አገልግሎት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ፡፡

በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጂቡቲ የወደቦችና ነጻ ቀጠና ባለስልጣን ሊቀ መንበር አቡበክር ኦማር ሃዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በዲክል እና ዳጎሩ መካከል ያለው 80 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ሂደትን አድንቀው፥ ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የቅርብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም እንደ ነዳጅ ያሉ አስፈላጊና መሰረታዊ የሆኑ ሸቀጦችን በፍጥነት ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ማፋጠን እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪ ሌሎች ሸቀጦችን በሚፈለገው ጊዜ ለማድረስ በሁለቱ ሃገራት በኩል በጋራ መስራት የሚቻልበትን አግባብ ማመቻቸት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.