Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡
በውይይቱ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጃፈር ሱፊያን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ እና ሌሎች በክልሉ የሚገኙ የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡
በመድረኩ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ÷ ተገደን በገባንበት ጦርነት የላቀ ድል ከማስመዝገብ ባለፈ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን በማረጋገጥ ፈጥነን ወደ ልማታችን መመለስ አብይ ትኩረታችን ነው በማለት ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጡና ፈጽሞ የማይደራደሩ መሆናቸውን በተግባር ማሳየታቸውን ነው ያነሱት፡፡
በመሆኑም በየደረጃ የሚገኙ አመራሮች ከድህረ ጦርነት በኋላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በሚገባ ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
አመራሩ በህልውና ዘመቻው የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለልማትና መልሶ ማቋቋም ተግባራት ሊጠቀምባቸው እንደሚገባም መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ የድህረ ጦርነት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ የፀጥታና ሰብአዊ ሁኔታዎች በብቃት ለመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.