Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓልን ምክንያት ያደረገ ጉዞ ማድረግ አይገባም – አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የመስቀል በአልን ምክንያት ያደረገ ጉዞ ማድረግ እንደማይገባ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ፡፡

ምክትል ርእስ መስተዳደሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በክልሉ በደማቁ የሚከበረውን የመስቀል በአልን ተከትሎ መሰባሰቦች ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት ምክንያት እንዳይሆን በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቤተሰብ የሚሰባሰበው በርካታ ህዝብ ዘንድሮ ባለበት እንዲያከብር አሳስበዋል ።

በተለይ የበዓላት ሰሞን የሰዎች እንቅስቃሴ መጨመር እና ጥግግት ባለባቸው ስፋራዎች በሽታውን የረሳ ተግባር መፈጸም ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

በኮሮና ቫይረስ ዋጋ የከፈሉት ሀያላን ሀገራት በተለይ በበአላት ወቅት በታየ መዘናጋት የስርጭት ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖባቸው መታየቱንም አቶ ርስቱ አንስተዋል፡፡

ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መስቀል የዘመን መለወጫ ያህል ክብር ያለው ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴቱን አስተሳስሮ ፤ በማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ ደግሞ ተናፋቂ መሰባሰቢያ በአል ነው ያሉም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ዘንድሮ እንዳለፉት ጊዜያት በመቀራረብ የሚከበር ሳይሆን ለስርጭቱ ምክንያት ባለመሆን ባሉበት ሆነው የሚደሰቱበት እንዲሆን መልእክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ከወዲሁ ለመሰቀል በአል መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል ።

በሀይለየሱስ መኮንን
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.